Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ ከማልታ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ ከማልታ አምባሳደር ሮናልድ ሚካሌፍ ጋር ተወያይተዋል።
አቶ ደመቀ መኮንን በዚህ ወቅት የማልታ መንግስት በቅርቡ ኤምባሲውን በኢትዮጵያ መክፈቱን አድንቀው ይህም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ብለዋል፡፡
ማልታ ለአፍሪካ እና አውሮፓ መግቢያ መሆኗን በመጥቀስ፥ ሀገራቱ ለጋራ ተጠቃሚነታቸው ያላቸውን እምቅ አቅም ማየት እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።
አያይዘውም ማልታ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ለመሆን ተቀባይነት በማግኘቷ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ማልታ በፀጥታው ምክር ቤት ቆይታዋ ለዓለም ሠላም እና መረጋጋት አዎንታዊ ሚና እንደምትጫወት ያላቸውን ዕምነትም ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ የማልታ አምባሳደር ሮናልድ ሚካሌፍ በበኩላቸው ÷ ሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊና የልማት ትብብራቸውን በማጠናከር በንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ትምህርት ላይ በትብብር እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ እና የማልታ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከፈረንጆቹ 1970ዎቹ ጀምሮ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version