አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ዜጎች የሚውል የ488 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አድርጓል።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ መንግሥት ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን የሰብዓዊ ድጋፋን በማስመልከት ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም÷ ድጋፉ በድርቅ ምክንያት አፋጣኝ ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ 4 ነጥብ 8 ሚሊየን ዜጎች የሚውል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አስቸኳይ የምግብ ድጋፍና የተመጣጠነ ምግብ ለሕጻናት እንደሚቀርብ በመግለጫው መነሳቱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!