Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 በጀት ዓመት 61 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 61 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በሰጡት መግለጫ÷ ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀውየ2014 በጀት ዓመት 61 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ጠቁመዋል፡፡
አሁን ላይም የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር 66 ሚሊየን መድረሱን ነው ዋና ስራ አስፈጻሚዋ የገለጹት፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም 45 በመቶ ያህሉ ተቋማቱ በግጭት ምክንያት አገልግሎት ሳይሰጡ 61 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version