Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የራስ ምታት መንስኤና መፍትሄዎቹ

 

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የራስ ምታት በየትኛውም የጭንቅላት /የራስ ክፍል/አካባቢ የሚከሰት የህመም አይነት ነው፡፡

ህመሙ የሚሰማዎት ጭንቅላትዎን ከፍሎ በአንዱ በኩል አሊያም በሁለቱም በኩል ሊሆን እንደሚችል የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ ፥ ህመሙ የመውጋት ወይም ለመግለፅ የሚያስቸግር አይነት ስሜት ሊኖረው ይችላል።

የራስምታት ቀስበቀስ ወይም በድንገት ሊመጣ የሚችል ሲሆን ፥ ህመሙ ከጀመረ በኋላ ለሰዓታት ወይም ለቀናት ሊቀጥል ይችላል።

የራስ ምታት በአብዛኛው ጊዜ የሚከሰተው ቀላል በሆኑ ምክንያቶች ሲሆን ፥ አንዳንድ ጊዜ ግን ለህይወት አስጊ በሆኑ ምክንያቶች ሊመጣ ይችላል።

በዚህም ሌላ ምክንያት የሌለው የራስምታት አይነት እና ምክንያት ያለው ራስ ምታት በመባል በሁለት ይከፈላሉ፡፡

1.ፕራይመሪ የራስ ምታት (ሌላ ምክንያት የሌለው የራስምታት አይነት)

ይህ የራስምታት አይነት የሚከሰተው በጭንቅላትዎ ውስጥ ያሉና ህመም እንዲሰማዎ የሚያደርጉ ክፍሎች ችግር ሲከሰትባቸው ወይም ከመጠን ያለፈ ስሜት በሚፈጠርበት ወቅት ነው።

በጣም ከሚታወቁትና ከዚህ የራስምታት አይነት ውስጥ የሚመደቡ የራስ ምታት አይነቶች  መካከል:-  ክላስተር ሄድኤክ ፣ማይግሬይን ሄድኤክ ፣ቴንሽን ሄድአክና የመሳሰሉት ሲሆኑእነዚህ የራስ ምታት አይነቶች የተወሰኑ የአኗኗር ዘይቤ ምክንቶች ሊያስነሱትና ሊያባብሱት ይችላሉ።

2.ሰከንደሪ ራስምታት (ምክንያት ያለው)

ይህ የራስምታት አይነት ሌላ ህመም ሊያመጣው  የሚችል  የመሰረታዊ ህመም ምልክት ሲሆን ለዚህ የራስ ህመም አይነት ምክኒያት ከሚሆኑ ህመሞች መካከል:-ድንገተኛ የሳይነስ ኢንፌክሽን ፣በጭንቅላት ውስጥ በደም መልስ ውስጥ ደም መርጋት ፣ በጭንቅላት ውስጥ የደም ቧንቧ መወጠር፤ መስፋት መከሰት ፣የጭንቅላት ውስጥ ዕጢ፣ በካርቦንሞኖኦክሳይድ መመረዝ፡- ለምሳሌ የከሰል ጭስ፣ የፈሳሽ ዕጥረት(ዲሃይድሬሽን) ፣የጥርስ ችግር ፣ የጆሮ ኢንፌክሽን ወዘተ…. ሊጠቀሱ ይችላሉ።

የህክምና ባለሙያ ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው?

እራስን መሳት ከተከሰተ፣የመቀበጣጠር ወይም የሰዎችን ንግግር መረዳት ያለመቻል ከተከሰተ፣ ከፍተኛ ትኩሳት ካለብዎ(ከ39° ሴ. ግሬድ በላይ )፣ባንድ በኩል ያለው የሰውነት ክፍልዎ የመደንዘዝ፣ የመስነፍ እና ያለመታዘዝ ምልክት ካለ፣የአንገት ያለመታጠፍ ችግር ካለ፣  የዕይታ ችግር ከገጠመዎ ፣የመናገር ችግር ከገጠመዎ ፣ የመራመድ ችግር ከገጠመዎ ፣ማቅለሽለሽና ትውከት የመሳሰሉት ከተከሰቱ የህክምና ባለሙያ ማማከር ያስፈልጋል፡፡

ለራስ ምታት ሊሰጡ የሚችሉ ህክምናዎች (ለማይግሬይን አይነት የራስ ምታት ህመሙን ሊያስታግሱ የሚችሉ መድሃኒቶች)

የማይግሬይን ራስምታትን ለመከላከል የሚሰጡ ህክምናዎች

ምንጭ :-ኸልዝ ላየን

Exit mobile version