Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ባይደን በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት እንደሚደግፉ የገለጹት ሀሳብ የኢትዮጵያ መንግስት አቋም ነው – አምባሳደር ስለሺ በቀለ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ሀገራቸው በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የተከሰተውን ግጭት ለመፍታት በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት እንደምትደግፍ መናገራቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ አስታውቀዋል።
 
77ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በአሜሪካ ኒውዮርክ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
 
በጉባኤው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዋሺንግተን በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት ለመፍታት በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት እንደምትደግፍ መናገራቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
 
አምባሳደር ስለሺ ፕሬዚዳንቱ በጉባኤው ጉዳዩን አስመልክተው የገለጹት ሃሳብ አሸባሪው ህወሓት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት ከሚያራምደው ሃሳብ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
Exit mobile version