Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ወልቂጤ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎችን አስተናግዷል።

ከምሳ በኋላ በተካሄደው የመጀመሪያ ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ በአዲሱ የወውድድር አመት ሁለተኛ ድሉን አስመዝግቧል፡፡

ክትፎዎቹ ባህርዳር ከተማን በተመስገን በጅሮንድ ድንቅ ግብ 1 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡

10 ሰአት ላይ በተካሄደውና ሰባት ጎሎች በተቆጠሩበት ጨዋታ ደግሞ ኢትዮጵያ መድን አርባምንጭ ከተማን 4 ለ 3 አሸንፏል።

በጨዋታው አሸናፊ ፊዳ እና ተመስገን ደረሰ (2) ለወላይታ ዲቻ ሲያስቆጥሩ፥ ብሩክ ሙሉጌታ፣ ኪቲካ ጅማ፣ አስጨናቂ ፀጋዬ እና ኢዮብ ገብረማርያም ለመድን የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version