Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሰሜን ኮሪያ አጭር ርቀት ሚሳኤል አስወነጨፈች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ አጭር ርቀት ሚሳኤል አስወነጨፈች።

ሚሳኤሉ ፒዮንግያንግ በዚህ ወር መጀመሪያ በድጋሚ የጀመረችው የሙከራ አካል ሲሆን፥ ወደ ጃፓን ባህር የተወነጨፈ ነው ተብሏል።

የጃፓን ባህር ሃይል በሃገሪቱ የባህር ክልል አቅራቢያ ሚሳኤል ማረፉን አስታውቋል።

ጎረቤት ደቡብ ኮሪያ በበኩሏ ተጨማሪ ሙከራዎች ካሉ በሚል ጉዳዩን እየተከታተልኩ ነው ብላለች።

የሃገሪቱ መከላከያ ባወጣው መግለጫ የኮሮና ቫይረስ የሃገራት ስጋት በሆነበት በዚህ ወቅት ሙከራ ማድረጉ ተገቢነት የሌለው መሆኑን ገልጿል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Exit mobile version