Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ መንግሥት ከሦስት ቀናት በፊት በጂቡቲ ጦር ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አወገዘ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግሥት ከሦስት ቀናት በፊት በጂቡቲ መከላከያ ሰራዊት ታጁራህ ክፍለ ጦር ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አወገዘ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በጥቃቱ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጾ፥ ለተጎጂ ቤተሰቦች ለጂቡቲ ህዝብ እና መንግስት መጽናናትን ተመኝቷል።

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የኢትዮጵያ መንግሥት ከጂቡቲ መንግሥት እና ሕዝብ ጎን እንደሚቆምም በመግለጫው ጠቅሷል።

አያይዞም መንግስት ከጂቡቲ ሪፐብሊክ መንግሥት ጋር በቀጠናው ሽብርተኝነትን ለመመከት በቅርበት ለመስራት ዝግጁ መሆኑንም ነው ያስታወቀው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version