Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የፕሪሚየር ሊጉ 7ኛ ሳምንት ቀሪ 4 ጨዋታዎች ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘሙ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ7ኛ ሳምንት ቀሪ 4 ጨዋታዎች ላልተወሰነ ጊዜ መራዘማቸው ተገለጸ።

ጨዋታዎቹ በድሬዳዋ ወቅታዊ የአየር ንብረት ምክንያት የመጫወቻ ሜዳው ለማጫወት ምቹ ባለመሆኑ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘማቸው ተገልጿል።

በዚህ መሰረት ዛሬ እና ነገ የሚካሄዱ ጨዋታዎች መራዘማቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል።

የተራዘሙት ጨዋታዎች ዛሬ 10:00 ሰዓት አርባምንጭ ከተማ – ከባህርዳር ከተማ
1:00 ሰዓት ሀዲያ ሆሳዕና – ከፋሲል ከነማ እንዲሁም

ነገ 10:00 ሰዓት አዳማ ከተማ – ከኢትዮጵያ ቡና

1፡00 ሰዓት ለገጣፎ ለገዳዲ – ከወላይታ ድቻ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ተራዝመዋል።

Exit mobile version