Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ደመቀ መኮንን ከኬንያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከኬንያው የውጭና የዳያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር አልፍሬድ ሙቱዋ ጋር ተወያዩ፡፡

ሚኒስትሮቹ በካርቱም እየተካሄደ ካለው የኢጋድ ስብሰባ ጎን ለጎን ባደረጉት ውይይት÷ የሀገራቱን የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ወዳጅነቱን ለማጠናከር ተስማምተዋል።

አቶ ደመቀ ኬንያ የሰላም ሂደቱ እንዲሳካ እንደ አገር እና በቀድሞ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኩል ላደረገችው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ለሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚነት መንግስት ቁርጠኛ መሆኑንም ነው ያስረዱት፡፡

ዶክተር አልፍሬድ እንደገለጹት÷ ኬንያ ለኢትዮጵያ ወዳጅነት የተለየ ቦታ እንደምትሰጥ በሰላም ሂደቱ የነበራት ሚና ማሳያ ነው፡፡

ሀገራቱ በኢኮኖሚ መስክ በተለይ በንግድና ኢንቨስትመንት መስኮች የተሻለና ትብብር መፍጠር እንደሚችሉ መገለጹንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version