Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፍሪካዊቷ ሞሮኮ ፖርቹጋል በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በዓለም ዋንጫው አፍሪካዊቷ ሞሮኮ ፖርቹጋልን 1 ለ 0 በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች፡፡
በኳታር የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሞሮኮ እና ፖርቹጋል ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡
በዚህም ሞሮኮ ፖርቹጋልን 1ለ0 በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን የተቀላቀለች ሲሆን÷ ሞሮኮ በአለም ዋንጫ ታሪክ ግማሽ ፍፃሜውን የተቀላቀለች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር መሆንም ችላለች፡፡
በሌላ የጨዋታ መርሐ ግብር ደግሞ እንግሊዝ ከፈረንሳይ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን የሚያከናውኑ ይሆናል፡፡
Exit mobile version