Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በዓለም ዋንጫው ሞሮኮ እና ፈረንሳይ ዛሬ በግማሽ ፍጻሜው ይጫወታሉ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት አንድ ጨዋታ ይደረጋል።
 
አፍሪካዊቷ ሞሮኮ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ከፈረንሳይ ጋር ለፍጻሜ ለመድረስ ትጫወታለች፡፡
 
ሁለቱ ቡድኖች በዓለም ዋንጫ በነጥብ ጨዋታ ሲገናኙ የምሽቱ የመጀመሪያቸው ይሆናል።
 
የጨዋታው አሸናፊ ከአርጀንቲና ጋር ለፍጻሜ የፊታችን እሑድ ይጫወታል።
 
ትናንት ምሽት በተደረገ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ አርጀንቲና ክሮሺያን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለፍጻሜ ማለፏ ይታወሳል፡፡
Exit mobile version