ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የአገልግሎት ጊዜያቸውን የጨረሱትን የእንግሊዝ አምባሳደር አሰናበቱ Melaku Gedif 1 year ago አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የአገልግሎት ጊዜያቸውን የጨረሱትን የእንግሊዝ አምባሳደር አለስተር ሜክፌልን አሰናብተዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ÷አምባሳደሩ በቆይታቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ላደረጉት ጥረት ምስጋና ማቅረባቸውንም ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡