Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለጋምቤላ ክልል የ36 ዘመናዊ ትራክተሮችና 150 የውሃ መሳቢያ ጀነሬተሮች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ለጋምቤላ ክልል 36 ዘመናዊ ትራክተሮችና 150 የውሃ መሳቢያ ጀነሬተሮች ድጋፍ አድርጓል፡፡

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ÷ ክልሉ ሰፊ መሬትና ውሃ የታደለ እንደመሆኑ የግብርና ሜካናይዜሽን ግብዓቶቹ መሬቱን ከውሃ ጋር በማገናኘት አደጋ የመቋቋም አቅምን ለማሳደግ ብሎም ምርታማነትን ለማምጣት ትልቅ እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በበኩላቸው ÷ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው ድጋፉ ክልሉ በግብርና ዘርፍ የጀመረውን ተግባር የሚያግዝና ከአርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ እየቀረበ ያለውን የሜካናይዜሽን ግብዓት አቅርቦት ጥያቄ የሚመልስ ነው ማለታውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version