አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ከደቡብ ጅግጅጋ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይት መድረኩ የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አያን አብዲ እና ሌሎች የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በውይይታቸውም ርዕሰ መስተዳድሩና አመራሮቹ ከጅግጅጋ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡