Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቀይ መስቀል ማኅበር ለትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት 15 ተሽከርካሪ ተበረከተ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አሥር አምቡላንሶችና አምስት ቀላል ተሽከርካሪዎችን ለማኅበሩ ትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስረከበ፡፡

ድጋፉ የተገኘው ከዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ፕሬዚዳንት አበራ ቶላ የሰብዓዊነት እሳቤን በሕብረተሰቡ ውስጥ ለማፅናት መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡

በማኅበሩ የትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ  ብርሃኑ መኮንን÷  ድጋፉ ሰብዓዊ አገልግሎቱን ለማስቀጠል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

ጽሕፈት ቤቱ ወደነበረበት ተመልሶ ሰብዓዊ አገልግሎቱን በክልሉ በስፋት እንዲያደርስ አጋር አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version