Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሚኒስትሮች ም/ቤት ዳግማዊት ሞገስ፣ ታከለ ኡማ፣ ኡመር ሁሴን እና ተፈሪ ፍቅሬን በክብር ሸኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዳግማዊት ሞገስ፣ ታከለ ኡማ፣ ኡመር ሁሴን እና ተፈሪ ፍቅሬን ዛሬ በክብር ሸኘ፡፡

በሽኝት መርሐግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት አራቱም የምክር ቤት አባላት ቀጣይ ጉዟቸው ስኬታማ እንዲሆንላቸው መመኘቱን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር፣ ኢንጅነር ታከ ኡማ የማዕድን ሚኒስትር፣ አቶ ኡመር ሁሴን የግብርና ሚኒስትር እንዲሁም አቶ ተፈሪ ፍቅሬ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር በመሆን ሀገራቸውን ሲያገለግሉ ነበር፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version