Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሔደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ጉባዔ በስካይላይት ሆቴል እየተካሔደ ነው፡፡

በጉባዔው ላይ÷ የኮንፌዴሬሽን ኦፍ አፍሪካ አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ሀማድ ካልካባ ማልቡም፣ የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅንና የአትሌቲክስ ፕሬዚዳንት ጀነራል ጃክሰን ቲዊ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትና የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ምክትል ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ተገኝተዋል፡፡

በተጨማሪም የፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እና የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን የጉባዔው አባላት እየተሳተፉ መሆኑን የአትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያላክታል፡፡

 

Exit mobile version