Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የጥምቀት በዓል በሠላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጥምቀት በዓል አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች በሠላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ።

በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱትን የፀጥታና ደኅንነት አባላት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የበዓሉ አስተባባሪዎች፣ የዕምነቱ ተከታዮች እና ወጣቶችን ግብረ ኃይሉ አመስግኗል፡፡

ነገ ወደ መንበራቸው የሚመለሱ ታቦታት በሠላም እንዲገቡ ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ግብረ ኃይሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

 

Exit mobile version