Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሶማሊያ ጦር በ39 የአልሸባብ አባላት ላይ እርምጃ ወሰደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያ ጦር በ39 የአልሸባብ ሽብር ቡድን አባላት ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡

ጦሩ ከዓለም አቀፍ የጸጥታ አጋሮች ጋር ባካሄደው የጸረ ሽብር ዘመቻ 39 የአልሸባብ ሽብር ቡድን አባላት መገደላቸውን የሀገሪቱ ምድር ጦር አዛዥ ጄነራል ሞሃመድ ታሃሊል ተናግረዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ አባላት በሙዱግ ግዛት ምዕራብ ሐራርዴሬ ወረዳ አካባቢ በተካሄደ የቅንጅት ዘመቻ መገደላቸውን የሶማሊያ ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡

Exit mobile version