Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአዋሽ አርባ የተመለከትነው የተቀናጀ የውጊያ ልምምድ ኢትዮጵያ ጦርነትን የሚያስቀር ሃይል መገንባቷን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዋሽ አርባ ዛሬ የተመለከትነው የተቀናጀ የውጊያ ልምምድ፥ ኢትዮጵያ ጦርነትን የሚያስቀር ሀይል መገንባቷን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።
 
ጠቅላይ ሚኒስት ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፥ በውጊያ ልምምዱ ዓየር ሃይል፣ ከባድ መሳሪያ፣ ልዩ ሃይል እና እግረኛ ተቀናጅቶ ውጊያን በአጭር የሚያስቀርባቸውን መንገዶች ተመልክተናል ብለዋል።
 
በየቀኑ አይናችንን ከምንፈልገው ህልም እና ተግባራችን እንድናነሳ የሚሹ ሃይሎች ስላሉ የጦር መኮንኖች ዋና ተግባር የሚሆነው ጦርነትን የሚያስቀር ሃይል መገንባት ነው ሲሉም አስገንዝበዋል።
Exit mobile version