Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሶማሊያ በሚካሄደው ቀጣናዊ መድረክ ለመሳተፍ ሞቃዲሾ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በምስራቅ አፍሪካ አልሸባብን የመዋጋት ዘመቻን ለማጠናከር በሶማሊያ በሚካሄደው ቀጣናዊ መድረክ ለመሳተፍ ሞቃዲሾ ገቡ፡፡

የመሪዎቹ ውይይት ለቀጣናዊ ችግሮች ቀጣናዊ መፍትሔ ለመስጠት ያለመ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

በተጨማሪም የአሸባሪውን አልሸባብ እንቅስቃሴ ለመግታት የቀጣናውን ሀገራት ትብብር ማጠናከርን ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ለዚህም የቀጣናው ሀገራት ሽብርተኝነትን ለማጥፋት በጋራ ማቀድ፣ ወቅቱን የጠበቀ ድጋፍ ማሰባሰብ እና በተለያየ መንገድ ሽብርተኝነትን መዋጋት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በአልአዛር ታደለ

Exit mobile version