Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
መሪዎቹ የተወያዩት በሶማሊያ ሞቃዲሾ ከተካሄደው ቀጠናዊ የጸረ ሽብር ውይይት መድረክ ጎን ለጎን ነው፡፡
 
በውይይታቸውም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
 
በተለይም የመሰረተ ልማት ትስስርን ማጠናከር፣ ኢንቨስትመንትን ማሳደግ እና ንግድ ላይ በትኩረት መምከራቸው ተመላክቷል፡፡
 
መሪዎቹ ከሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ባለፈ በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውም ተጠቁሟል፡፡
 
በአልአዛር ታደለ
Exit mobile version