Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቦረና ዞን ድርቁን ተከትሎ ከ7 ሺህ 800 በላይ ተማሪዎች ትምህርት አቋረጡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በቦረና ዞን ድርቁን ተከትሎ ከ7 ሺህ 800 በላይ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ማቋረጣቸውን የቦረና ዞን ትምህርት ጽኅፈት ቤት ገለፀ።

የፅህፈት ቤቱ ሃላፊ ተስፋዬ ወ/ሚካኤል እንደገለፁት÷ በዞኑ ባሉ 490 ትምህርት ቤቶች በመማር ላይ የሚገኙ የ174 ሺህ ተማሪዎች ውጤትም ቀንሷል።

ተማሪዎቹን ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ የምገባ ፕሮግራም እየተደረገ እንዳለ የገለፁ ሲሆን÷ምገባውን ለማስቀጠል ክልሉ ወደ 45 ሚሊየን ብር መመደቡን አመላክተዋል።

አሁን ላይ በ80 ትምህርት ቤቶች የመማሪያ፣ የማደሪያ እና የምገባ አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በዞኑ ድርቁን ተከትሎ በተስተዋለው ከባድ ንፋስ 47 ትምህርት ቤቶች መፍረሳቸው ገልፀው ለመልሶ ግንባታም የክልሉ መንግስት 5 ሚሊየን ብር መድቧል ነው ያሉት፡፡

21 ትምህርት ቤቶችም በፍጥነት እንዲገነቡ እንቅስቃሴ ተጀምሯል ተብሏል።

እስካሁን ድርቁን ተከትሎ የተዘጉ ትምህርት ቤቶች የሉም ያሉት ሃላፊው በፈረሱት ቦታ ዳስ ተጥሎ እንዲማሩ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

በታሪኩ ለገሰ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version