Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በደቡብ ክልል በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ 2 ሚሊየን ዜጎች አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ 2 ሚሊየን ዜጎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጥሪ አቅርቧል፡፡
 
በደቡብ ክልል 342 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የነበረ ምርት በዝናብ እጥረት ምክንያት ከጥቅም ውጭ እንደሆነ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ምክር ቤት በዳሰሳ ጥናት ማረጋገጡ ተጠቁሟል።
 
የዝናብ መቆራረጥና በቂ ስርጭት አለመኖር በክልሉ ድርቅ እንዲከሰት ምክንያት መሆኑን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊ ኡስማን ሱሩር ተናግረዋል፡፡
 
ለዚህ ችግር ፈጥኖ መድረስ እንደሚያስፈልግ ነው ሃላፊው አጽንኦት የሰጡት፡፡
 
በክልሉ ለ2 ሚሊየን ዜጎች አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ያነሱት አቶ ኡስማን÷ መንግስታዊም ይሁን መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን ዴሬቴድ ዘግቧል፡
Exit mobile version