Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አመራር ወቅቱንና ኃላፊነታቸውን የሚመጥን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አመራር ወቅቱንና ኃላፊነታቸውን የሚመጥን መሆኑን አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ጊዜው የጋራ አመራር የሚጠይቅ መሆኑን እንዳረጋገጡላቸው በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ስለ ኮቪድ19 ወቅታዊ መረጃዎችን መስጠታቸውን በመጥቀስ የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት የዓለም የጤና ድርጅት በሚያከናውነው ተግባር ምስጋና አቅርበውላቸዋል።

አያይዘውም አመራራቸው ወቅቱንና ኃላፊነታቸውን የሚመጥን መሆኑን አውስተዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version