Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዕውቁ ሩሲያዊ ጠፈርተኛ ከጠፈር ላይ ሆኖ ያነሳውን የዳሎል ምሥል ለኢትዮጵያውያን አስረከበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዕውቁ የሩሲያዊ ጠፈርተኛ ሰርጌይ ኩድ ስቨርቺኮቭ ከጠፈር ላይ የወሰደውን የዳሎልን ምሥል በአዲስ አበባ ተገኝቶ ለኢትዮጵያውያን አስረክቧል።

ሰርጌይ ኩድ ስቨርቺኮቭ  ÷ በ2012 ዓ.ም በዓለም አቀፉ የጠፈር ማዕከል 185 ቀናትን  ያሳለፈ ጠፈርተኛ  መሆኑ ተገልጿል፡፡

በነገው ዕለትም በአዲስ አበባ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተገኝቶ ለተማሪዎች፣ ለመምህራንና ለተመራማሪዎች ገለጻ ያደርጋል ተብሏል፡፡

Exit mobile version