ዕውቁ ሩሲያዊ ጠፈርተኛ ከጠፈር ላይ ሆኖ ያነሳውን የዳሎል ምሥል ለኢትዮጵያውያን አስረከበ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዕውቁ የሩሲያዊ ጠፈርተኛ ሰርጌይ ኩድ ስቨርቺኮቭ ከጠፈር ላይ የወሰደውን የዳሎልን ምሥል በአዲስ አበባ ተገኝቶ ለኢትዮጵያውያን አስረክቧል።
ሰርጌይ ኩድ ስቨርቺኮቭ ÷ በ2012 ዓ.ም በዓለም አቀፉ የጠፈር ማዕከል 185 ቀናትን ያሳለፈ ጠፈርተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በነገው ዕለትም በአዲስ አበባ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተገኝቶ ለተማሪዎች፣ ለመምህራንና ለተመራማሪዎች ገለጻ ያደርጋል ተብሏል፡፡