Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

“መጋቢት 24 የመንግስትን ስርዓት በሴራና ሃይል የመቀየር አስተሳሰብን የዘጋ ታሪካዊ ቀን ነው” – የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በአምቦና ሌሎች ከተሞች ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ፡፡

የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወዲህ በክልሉ የተመዘገቡ ድልና ስኬቶችን የሚያንጸባርቁ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡

በድጋፍ ሰልፉ “መጋቢት 24 የመንግስትን ስርዓት በሴራና በሃይል የመቀየር አስተሳሰብን የዘጋ ታሪካዊ ቀን ነው፣ ሌብነትና ስንፍና የመጋቢት 24 ጠላቶች ናቸው የሚሉና ሌሎች መፈክሮች ተደምጠዋል፡፡

በድጋፍ ሰልፉ በርካታ ቁጥር ያላቸው የከተማዋ እና አካባቢው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

Exit mobile version