Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በጅማ ከተማ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ከተማ ለ2 ሺህ ሰዎች የጎዳና ላይ የኢፍጣር ሥነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡

ስነስርዓቱ በቀርጫሼ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እንዲሁም በጅማ ከተማና ዞን አስተዳደር የተዘጋጀ ነው፡፡

በአፍጥር ስነ-ስርዓቱ የከተማው አቅመ ደካሞችን ጨምሮ በተለያዩ ደረጃ ያሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

የሰቃ ወረዳ ኢማም ሼህ ወዚር መሃመድ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት÷ የረመዳን ወር ያላቸው ለሌላቸው የሚያካፍሉበት የተቀደሰ ወር ነው፡፡

በመሆኑም በተቀሩት የፆም ቀናት የእስልምና እምነት ተከታዮች በዘር በሃይማኖት ሳይለዩ አቅመ ደካሞች በመርዳት እንድያሳልፉ መልክት አስተላልፈዋል።

በሙክታር ጣሓ

Exit mobile version