Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ተቋማት ለገበታ ለትውልድ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ተቋማት ለገበታ ለትውልድ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውን እንደቀጠሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅኅፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በዚህም መሠረት በሦስተኛው ዙር ድጋፍ ያደረጉ ተቋማትን ዝርዝር ፅህፈት ቤቱ ይፋ አድርጓል።

አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ 267 ሚሊየን 50 ሺህ ብር፣ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ 50 ሚሊየን ብር፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 50 ሚሊየን ብር፣ ሰይድ ያሲን ኃ.የተ. የግል ኩባንያ 20 ሚሊየን ብር፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር 12 ሚሊየን 707 ሺህ ብር ፣ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት 10 ሚሊየን 681 ሺህ 559 ብር ፣ አልሳም ኃ.የተ. የግል ኩባንያ 10 ሚሊየን ብር፣ ታፍ ኦይል 10 ሚሊየን ብር ፣ አምደሁን ጀነራል ትሬዲንግ 10 ሚሊየን ብር ፣ ኤም ደብልዩ ኤስ ትሬዲንግ 10 ሚሊየን ብር ፣ ኤም ሲ ጂ ኮንስትራክሽን 10 ሚሊየን ብር እንዲሁም ጎልድ ውሃ 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version