Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአቶ አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያየ።

በውይይቱ አቶ አህመድ ሺዴን ጨምሮ የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ጠቃሚ ውይይት ማድረጋቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) አስታውቀዋል።

ውይይቱ ከፀደይ ወቅት ስብሰባ ጎን ለጎን የተካሄደ ሲሆን ከዓለም ባንክ፣ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) እና ከዓለም አቀፉ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን (አይ ኤፍ ሲ) ፕሬዚዳንቶች፣ ዋና ዳይሬክተሮች እና ዳይሬክተሮች ጋር መደረጉንም ነው ያስታወቁት።

በውይይቱም የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች፣ ምጣኔ ሀብት፣ ፋይናንስ እና አጋርነትን በተመለከተ ለኢትዮጵያ ልማት ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ገለፃ መቅረቡም ተመላክቷል።

Exit mobile version