Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ከተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) የኢትዮጵያ ተወካይ አቡባካር ካምፖ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም አቶ ሙስጠፌ ዩኒሴፍ በሶማሌ ክልል እርዳታ ለሚሹ ዜጎች እያከናወነ የሚገኘውን ስራ አድንቀዋል፡፡
በቀጣይ ዩኒሴፍ በክልሉ የሚያከናውናቸውን ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውንም አቶ ሙስጠፌ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
Exit mobile version