Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሉሜ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ10 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ10 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

የሉሜ ወረዳ የትራፊክ ደህንነት አስተባባሪ ኢንስፔክተር ተክልየ ታምሩ እንደገለጹት÷አደጋው ዛሬ ጠዋት ከአረርቲ ከተማ ወደ አዳማ ከተማ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ከቆመ መኪና ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡

በአደጋው 10 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን የገለጹት ኢንስፔክተሩ÷ በአከባቢው ከዚህ በፊት መሰል አደጋዎች መከሰታቸውን ጠቁመዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር እንደሆነ መገለጹንም ከሉሜ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version