Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ደመቀ ከኡጋንዳ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ጅቡቲ ፕሬዚዳንቶች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከኡጋንዳ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ጅቡቲ ፕሬዚዳንቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በአሚሶም ተልዕኮ የተሳተፉ ሀገራት መሪዎች ስብሰባ በኡጋንዳ እንቴቤ እየተካሄደ ነው፡፡

አቶ ደመቀ ከኡጋንዳ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ፣ ከኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐመድ እና ከጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኡመር ጊሌ ጋር ነው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የመከሩት፡፡

ጉባዔው ኢትዮጵያ እና ሌሎች አካላት ለሶማሊያ መረጋጋት ላበረከቱት ሚና አድናቆቱን ገልጿል።

ውይይቱ በኡጋንዳ እየተካሄደ በሚገኘው በአሚሶም ተልዕኮ የተሳተፉ ሀገራት መሪዎች ስብሰባ ጎን ለጎን መደረጉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የመሪዎች ጉባዔው የኤቲኤምኤስ ተልዕኮ አፈፃፀም ላይ የተገኙ ውጤቶችን ለመገምገም እና የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎችን ባከበረ መልኩ የአሚሶም ቅነሳ እቅድን ለመገምገም ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡

አቶ ደመቀ ባለፉት አራት ቀናት በታንዛኒያ፣ ኮሞሮስ እና ብሩንዲን ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ፥ ከሦስቱ እህትማማች አፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የሰላምና የጸጥታ ችግሮች ለመፍታት የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

 

 

Exit mobile version