Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በግርማ የሺጥላ ግድያ የተሰማቸውን ሀዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ግርማ የሺጥላ ግድያ የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ፥ “በወንድሜ በአቶ ግርማ የሺጥላ ድንገተኛ ሞት የተሰማኝ ሐዘን በጣም ጥልቅ ነው” ብለዋል፡፡

አቶ ግርማ በሃሳብ ልዕልና የሚያምኑ፣ ለሀገራዊ አንድነትና ለሕዝቦች ወንድማማችነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊ እንደነበሩም አውስተዋል፡፡

ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ÷ ለሥራ ባልደርቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

በተመሳሳይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በግርማ የሺጥላ ግድያ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል፡፡

በመግለጫውም ፥ ጽንፈኞች በፈጸሙት አስነዋሪ ተግባር የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የብልፅግና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወንድም ግርማ የሺጥላ ህይወታቸው ማለፉን ሲንሰማ ከፍተኛ ሀዘን ተሰምቶናል ብለዋል ::

ጽንፈኝነት ለማንም የማይጠቅም የዘመናችን በሽታና የአንድነታችን ነቀርሳ ነው ያለው ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ፥ ሁላችንም አጥብቀን ልንታገለውና ልንኮንነው ይገባል ብሏል።

አቶ ግርማ የሺጥላ ለአማራ ክልል እንዲሁም ለሀገራቸው ህዝቦች ልማትና እድገት ደከመኝ ታከተኝ ሳይሉ ሲለፉና ሲታክቱ የነበሩ ታማኝ የህዝብ ልጅ እንደነበሩም አንስቷል፡፡

Exit mobile version