Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ከኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ብሄራዊ ሙዚየምን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ እና የኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንሲያ ማርኩዌዝ ብሄራዊ ሙዚየምን ጎብኝተዋል፡፡

በኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት የተመራው የልዑካን ቡድን ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋርም ተወያይቷል፡፡

በነበራቸው የቆይታም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየምን ጨምሮ ሌሎች በአዲስ አበባ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎችን ተዟዙረው ጎብኝተዋል፡፡

የጉብኝቱ መርሐግብር በቱሪዝም ሚኒስቴር እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጋራ ትብብር የተዘጋጀ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version