Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አምባሳደር ፍጹም አረጋ ከካናዳ የትራንስፖርት ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

 

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 2 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ ከካናዳ የትራንስፖርት ሚኒስትር እና የፓርላማ አባል ዑመር አልጀብራ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም የበረራ ግንኙነቶችን ማሻሻል በሀገራቱ ብሎም በሁለቱ በአህጉራት መካከል የንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ቱሪዝም እና የባህል ልውውጥን ከማሳደግ አንጻር ያለውን ጠቀሜታ በተመለከተ መክረዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ከኢትዮጵያ ካናዳ የሚያደርገውን በረራ ማስፋት በሚቻልበት አግባብ ላይ መምከራቸውንም አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት ከአዲስ አበባ ቶሮንቶ በረራ ያደርጋል።

Exit mobile version