Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከሀይማኖት አባቶች ጋር በመሆን በመዲናዋ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 26 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከሀይማኖት አባቶች ጋር በመሆን በመዲናዋ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

የሀይማኖት አባቶቹ በቅርቡ የተጀመረውን የመስቀል አደባባይ መልሶ ግንባታን ጨምሮ፥ የአድዋ ማዕከል፣ የሸገር ቤተ መጽሐፍት እና የቤተ መንግስት መኪና ማቆሚያ ስፍራን ጎብኝተዋል።

ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለሀይማኖት አባቶቹ ስለ ፕሮጀክቶቹ ግንባታ ገለፃ አድርገውላቸዋል።

የፕሮጀክቶቹ ግንባታ በተፋጠነ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ከአዲስ አባበ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version