Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የዒድ አልፈጥር በዓል መልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለ1 ሺህ 441ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል መልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው ላይ ባስተላፉት መልዕክት “ለመላው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ወገኖቼ መልካም የኢድ አል ፈጥር በዓል እመኛለሁ”።

ሙስሊሙ ማህበረሰብ በታላቁ የረመዳን ጾም ያሳየውን መተሳሰብና አንድነት በማጠናከር የሚገጥሙንን ችግሮችና ፈተናዎች ሁሉ በጋራ እንደምንፈታ እምነቴ የላቀ ነው ብለዋል በመልዕክታቸው።

1 ሺህ 441ኛው ኢድ አል ፈጥር ነገ እሁድ ይከበራል።

Exit mobile version