Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በፕሪሚየር ሊጉ ሲዳማ ቡና ባሕር ዳር ከተማን 2 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ11ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ባሕር ዳር ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክቷል፡፡

ቀን 12 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ የሲዳማ ቡናን ግቦች ጊት ጋትኩት እና ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን አስቆጥረዋል፡፡

በጨዋታው የባሕርዳር ከተማው ተከላካይ ያሬድ ባዬ በፈጸመው ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል፡፡

በተመሳሳይ ቀን 9 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ቡና እና ሀድያ ሆሳዕና ያካሄዱት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡

Exit mobile version