Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ስለሽ ከሱዳን አቻቸው ፕሮፌሰር ያሲር አባስ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ስለሽ በቀለ ከሱዳን አቻቸው ፕሮፌሰር ያሲር አባስ ጋር ተወያዩ።

በቪዲዮ ኮንፈረንስ በተካሄደው በዚህ ውይይት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የሶስትዮሽ ድርድር ማስቀጠል በተመለከተ መክረዋል።

የስብሰባውም አጀንዳ የሶስትዮሽ ድርድሩ እንደገና የሚጀምርበት፣ ስለሚከናወንበት የስነ ስርዓት ጉዳዮች እና ግድቡን በተመለከተ የሀገራቱ ዋናዋና ጉዳዮች እና ሃሳቦችን የተመለከተ ነበር።

ሁለቱ ወገኖች የሁለትዮሽ ስብሰባዎችን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ የሶስትዮሽ ስብሰባው በቶሎ እንዲጀመር ስለማመቻቸት መስማማታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም ሁለቱ ወገኖች ከድርድሩ ጋር የተያያዙ ያልተፈቱ ዋናዋና ጉዳዮችን በተመለከተም ሃሳብ ተለዋውጠዋል።

Exit mobile version