አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ) ወለጋ፣ አርሲ እና ዲላ ዩኒቨርሲቲዎች በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሀ ግብር በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠነኗቸውን ተማሪዎች እያስመቁ ነው።
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ፣ በሁለተኛ ድግሪ እና በፒ ኤች ዲ ያሰለጠናቸውን 1ሺህ 374 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው ፡፡
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የሴኔት አባላት ፣ የተመራቂ ወላጆች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በተመሳሳይም አርሲ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንሰ ኮሌጅ በተለያዩ መሰኮች ያሰለጠናቸውን 214 ተማሪዎች አስመርቋል።
በምረቃ መርሃ ግብሩ የጤና ሳይንስ ኮሌጁ ዲን ዶ/ር ዲዳ ባቱ ፣ኮሚሸነር ደራርቱ ቱሉ ፣የተመራቂ ወላጆች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
እንዲሁም የዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ሲያስምራቸው የቆዩ 434 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው፡፡
በገላና ተስፋ፣ኦሊያድ በዳኔ እና ሂርጶ ሺቦ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!