Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

135 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 135 ኢትዮጵየዊያን በዛሬው እለት ከሳኡዲ አረቢያ መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከሳዑዲ ተመላሽ ኢትዮጵያውያኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፈያ ሲደርሱ የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ሀላፊዎች በቦታው ተገኘተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የዛሬዎቹን ጨምሮ በሳምንቱ ውስጥ ከሳኡዲ አረቢያ ወደ አገራቸው የተመለሱ ዜጎቻችን ቁጥር 389መድረሱንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

ባሳለፍነው ሀሙስ 118 ኢትየጵያዊን ከሳኡዲ አረቢያ መመለሳቸው የሚታወስ ሲሆን፥ በተመሳሳይ ባለፈው ማክሰኞም 136 ዜጎች ከሳኡዲ አረቢያ መመለሳቸው አይዘነጋም።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version