Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል አገልግሎት ሙሉ በሙሉ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

በሲስተም ችግር ምክንያት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም በቅርንጫፎች፣ በኢንተርኔት ባንኪንግ፣ በሞባይል ባንኪንግ፣ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሞ እንደነበር ባንኩ መግለጹ ይታወቃል፡፡

በቅርንጫፍ እና በኤቲኤም የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀደም ብለው መጀመራቸው ይታወሳል፡፡

አሁን ላይም በዲጂታል የሚሰጡ የባንክ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ መጀመራቸውን ነው ባንኩ ያስታወቀው፡፡

ባንኩ ደንበኞቹ በትዕግስት ስለጠበቁ አመስግኖ ፥ ለተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎልም ይቅርታ ጠይቋል፡፡

Exit mobile version