Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል  ሆነው ተሾሙ።

አምባሳደሩ  በድጋሚ ቃል አቀባይ ሆነው መሾማቸውን  ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት  ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

በቅርቡም በግብጽ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ሲሰሩ ነበር።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በተለያዩ ሀገራት በአምባሳደርነት ከማገልገላቸው በፊትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል።

Exit mobile version