Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የናይጄሪያ ልዑክ በኢትዮጵያ የመስኖ ስንዴ ልማት ዘርፍ የልምድ ልውውጥ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አመራሮችንና ባለሙያዎችን ያካተተው የናይጄሪያ ልዑክ በኢትዮጵያ በመስኖ ስንዴ ልማት ላይ የልምድ ልውውጥ አድርጓል፡፡

ከልምድ ልውውጡ በተጨማሪ ልዑኩ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አቢቹፍ ኛአ እና ቅምቢት ወረዳዎች በበኩታ ገጠም እየለማ ያለ የመስኖ ስንዴ ልማት እንቅስቃሴን ተመልክቷል፡፡

የግብርና ሚኒስትር ዴዔታ መለስ መኮንን (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳስረዱት÷ በመስኖ ስንዴ ልማት ዘንድሮ 3 ሚሊየን ሄክታር በማልማት 120 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የስንዴ ልማት ሥራው ከውጪ የሚገባውን ስንዴ ማስቀረቱን ገልጸው፤ የምግብና ስርዓተ-ምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ረገድም የአርሶ አደሩን ገቢ ለማሳደግ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት እና ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

Exit mobile version