Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ልዑክ ኮምቦልቻ ገባ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ የፌደራል መንግሥት እና የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ ኮምቦልቻ ገብቷል፡፡

ልዑኩ ኮምቦልቻ ከተማ ሲደርስ በአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና በከተማው ነዋሪዎች አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት በኮምቦልቻ በሚኖራቸው ቆይታ በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል፡፡

በምክትል ጠቅላይ  ሚኒስትር ተመስገን የተመራው ልዑክ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህን ጨምሮ ሌሎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ ነው፡፡

በፍሬ ሕይወት ሰፊው

Exit mobile version