Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

4ኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ ለሶስተኛ ጊዜ ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አራተኛው የኢትዮጵያ ህዝብና ቤት ቆጠራ ለሶስተኛ ጊዜ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ባካሄዱት የጋራ ስብሰባ ወሰኑ።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌደሬሽን ምክር ቤት በዛሬው እለት የጋራ ስብሰባ አካሂደዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አዳራሽ በተካሄደው በጋራ ስብሰባቸውም 4ኛውን የህዝብና ቤት ቆጠራ ለሶስተኛ ጊዜ ለማራዘም የተዘጋጀውን የውሳኔ ሀሳብ ተመልክተዋል።

ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜ የተራዘመው የህዝብና ቤት ቆጠራ አሁንም በኮሮናቫይረስ ምክንያት ለህዝብ ጤናና ደህንነት ሲባል ለሶስተኛ ማራዘም ማስፈለጉን ተገልጿል።

የምክር ቤቶቹ አባላት በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ ቆጠራው እንዲራዘም የቀረበውን የውሳኔ ሃሳቡን በ5 ተቃውሞ፣ በ13 ድምጸ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቀውታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version