Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ የደረሱ ሰብሎችን የሚሰበስቡ አርሶ አደሮችን አበረታቱ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት በአርሶ አደሮች ማሳ በመገኘት የደረሱ ሰብሎችን ሰብስበዋል።

በዚህም አርሶ አደሮች የደረሱ ሰብሎችን በወቅቱ በመሰብሰብ የሚያጋጥመውን የእህል ብክነት ለመከላከል በትጋት እንዲሰሩ አበረታተዋል።

በተጨማሪም ሀገር ለመመገብ ከዘር እስከ መኸር ለሚተጉ የሀገሪቱ አርሶ አደሮች ምስጋና ማቅረባቸውን በፌስ ቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

Exit mobile version